• Skip to main content

ChronologicalGospel.net

The Chronological Gospel

  • Why Teach the Bible Chronologically?
  • Chronological Gospel – What is it?
  • Lessons
  • Instructions for Translators
  • Chronological Teaching Videos
  • Testimonies
  • Hope Church

Amharic Lesson 01

ትምህርት 1

– እዚህ የመጣሁት ለምንድነው?

– እዚህ የመጣሁት ልጐዳችሁ ነው?

– አይደለም።

– እዚህ የመጣሁት ቤተሰባችሁን ወይም ጓደኞቻችሁን ልጐዳ ነው?

– አይደለም።

– እዚህ የመጣሁት መሬታችሁን ልወስድ ወይም ከብቶቻችሁን ልሰርቅ ነው?

– አይደለም።

– ታዲያ እዚህ የመጣሁት ለምንድነው?

– እዚህ የመጣሁት ለአንድ ጉዳይ ብቻ ነው።

– እዚህ የመጣሁት በዚህ ዓለም እጅግ አስፈላጊ የሆነውን መልእክት ልነግራችሁ ነው።

– እዚህ የመጣሁት የእግዚአብሔርን መልእክት ልነግራችሁ ነው።

– እዚህ የመጣሁት የነጮችን መልእክት ልነግራችሁ አይደለም። 

– እዚህ የመጣሁት የጥቁር ሕዝቦችን መልእክት ልነግራችሁ አይደለም።

– እዚህ የመጣሁት የእግዚአብሔርን መልእክት ብቻ ልነግራችሁ ነው።

– መሪያችሁ ለአስፈላጊ ጉዳይ ሁላችሁንም ቢጠራችሁ ትመጣላችሁ አይደል?

– አዎን ትመጣላችሁ።

– ለምንድን ነው የምትመጡት?

– ምክንያቱም መሪያችሁ የሚነግራችሁ መልእክት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

– የመሪ መልእክት አስፈላጊ ነው ነገር ግን ከመሪ መልእክት እጅግ የሚበልጥ መልእክት አለ።

– ከመሪ መልእክት የሚበልጥ መልእክት የማን መልእክት ነው?

– የእግዚአብሔር መልእክት ነው።

– በዚህ ዓለም እጅግ አስፈላጊ የሆነው መልእክት የማን መልእክት ነው?

– የእግዚአብሔር መልእክት ነው።

– የእግዚአብሔር መልእክት በዚህ ዓለም እጅግ አስፈላጊ መልእክት የሆነው ለምንድን ነው?

– ምክንያቱም እግዚአብሔር በፍጹም ስለማይዋሽ ነው።

– እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እውነትን ብቻ ስለሚናገር ነው።

– ከሰዎች መካከል ዋሽቶ የማያውቅ አለ?

– የለም ሁሉም ሰው ዋሽቷል።

– ከእናንተ መካከል ዋሽቶ የማያውቅ አለ?

– የለም ሁላችሁም ዋሽታችኋል።

– ከዚህ በፊት እኔም ዋሽቼአለሁ።

– ነጭ ሁሉም ዋሽቶአል።

– ጥቁር ሁሉም ዋሽቶአል።

– ሁሉም ሰው ዋሽቶአል።

– ዋሽቶ የማያውቅ ማን ነው?

– እግዚአብሔር ብቻ ነው።

– እግዚአብሔር ዋሽቶ ስለማያውቅ፤ እውነቱን ሊነግረን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።

– እግዚአብሔር በፍጹም ዋሽቶ ስለማያውቅ ስለ ራሱ እውነቱን ሊነግረን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።

– እግዚአብሔር ፈጽሞ ዋሽቶ ስለማያውቅ የእግዚአብሔር መልእክት በዚህ ዓለም እጅግ አስፈላጊ መልእክት ነው።

– ለወንዶች የእግዚአብሔር መልእክት በእርሻ ቦታ ከመሥራት የበለጠ አስፈላጊ ነው።

– ለምን?

– ምክንያቱም ወንዶችን ሁሉ ከሞት ማዳን የሚችለው የእግዚአብሔር መልእክት ብቻ ስለሆነ ነው።

– ለሴቶች የእግዚአብሔር መልእክት ምግብ ከማብሰል የበለጠ አስፈላጊ ነው።

– ለምን?

– ምክንያቱም ሴቶችን ሁሉ ከሞት ማዳን የሚችለው የእግዚአብሔር መልእክት ብቻ ስለሆነ ነው።

– ለልጆች የእግዚአብሔር መልእክት ከጨዋታ የበለጠ አስፈላጊ ነው።

– ለምን?

– ምክንያቱም ልጆችን ሁሉ ከሞት ማዳን የሚችለው የእግዚአብሔር መልእክት ብቻ ስለሆነ ነው።

– የእግዚአብሔር መልእክት የሚገኘው የት ነው?

– የእግዚአብሔር መልእክት የሚገኘው በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ ነው።

– የእግዚአብሔር መጽሐፍ ምን ይባላል?

– የእግዚአብሔር መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ይባላል።

– የእግዚአብሔር መልእክት በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ እንዴት ተጻፈ?

– እግዚአብሔር ራሱ የራሱን መልእክት በመጽሐፍ ሊጽፍ ይችል ነበር ሆኖም ግን ይህን አላደረገም።

– ከረጅም ዘመናት በፊት እግዚአብሔር ጥቂት ሰዎችን መረጠ ቃሉንም በእነዚህ ሰዎች ልብ ውስጥ አኖረ።

– ከዚያም እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ ጻፉት።

– እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ የጻፉት የራሳቸውን ቃል ነው?

– የራሳቸውን ቃል አይደለም።

– እነዚህ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች የራሳቸውን ቃል አልጻፉም።

– እነዚህ ሰዎች የጻፉት የእግዚአብሔርን ቃል ነው።

– እነዚህ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች የጻፉት በትክክል የእግዚአብሔርን ቃል ነው።

– እግዚአብሔር ቃሉን በእርሱ መጽሐፍ እንዲጽፉ አርባ ያህል ሰዎችን መረጠ።

– እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት ሰዎች ሁሉም የኖሩት በተመሳሳይ ጊዜ ነበር?

– አይደለም።

– እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት ሰዎች ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ አልኖሩም።

– ሁሉንም የእግዚአብሔር ቃል ጽፎ ለማጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ፈጀ?

– እነዚህ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች ቃሉን ጽፈው ለማጠናቀቅ 1,600 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል።

– እነዚህ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲጽፉ የመረጣቸው ሰዎች እነማን ነበሩ?

– እግዚአብሔር ቃሉን እንዲጽፉ የመረጣቸው ሰዎች አይሁዶችና አንድ ግሪካዊ ነበሩ።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በምን ቋንቋ ነበር? 

– በአይሁዶችና በግሪኮች ቋንቋ ነበር።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በእንግልእኛ ነበር?

– አይደለም

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በአማርኛ ነበር?

– አይደለም።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በኦሮምኛ ነበር? 

– አይደለም።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በራሳቸው ቋንቋ ነበር።

– ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃሉን እንዲጽፉ የመረጣቸው ሰዎች አይሁዶችና አንድ ግሪካዊ ስለነበሩ ነው።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የጻፉት በአይሁዶችና በግሪኮች ቋንቋ ነበር።

– ከብዙ ጊዜ በኋላም ሌሎች ሰዎች ወደ አይሁድ ምድር መጡ የእግዚአብሔርን ቃል አነበቡ፤ ወደ የራሳቸውም ቋንቋ ተረጐሙት።

– የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሟል።

– የእግዚአብሔር ቃል በእናንተም ቋንቋ ተተርጐሟል፤ እየተተረጐመም ነው።

– በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መካከል ስንቱ እውነት ነው?

– ሁሉም እውነት ነው።

– በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል እንዴት እውነት ሊሆን ቻለ?

– ምክንያቱም እግዚአብሔር በፍጹም ስለማይዋሽ ነው።

– እግዚአብሔር እውነትን ብቻ ስለሚናገር ነው።

– በእግዚአብሔር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን የእግዚአብሔርን ቃሎች የምናምነው ለምንድነው?

– ምክንያቱም እግዚአብሔር በፍጹም ስለማይዋሽ ነው።

– እግዚአብሔር እውነትን ብቻ ስለሚናገር ነው።

– ሁልጊዜ እውነትን ብቻ የሚናገር ማን ነው? 

– እግዚአብሔር ነው

– እኔ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቃል አንብቤ ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን አውቄያለሁ።

– እናንተም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰሙ የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ታውቃላችሁ።

– የዚህ ምክንያቱ እግዚአብሔር በፍጹም ስለማይዋሽ ነው። 

– የዚህ ምክንያቱ እግዚአብሔር እውነትን ብቻ ስለሚናገር ነው።

– እግዚአብሔር ብዙ የሚነግረን ነገር አለው። 

– ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ለእናንተ ለማስተማር ብዙ ቀን ያስፈልጋል።

– አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡

– የእርሻን ሥራ ለማወቅ ምን ያህል ቀናት ይወስዳል?

– አዎ ብዙ ቀናት ይወስዳል።

– የእርሻን ሥራ ለማወቅ ብዙ ቀናት የሚወስደው ለምንድን ነው?

– ምክንያቱም ስለ አስተራረስ ልናውቃቸው የሚገቡን ብዙ እውነቶች ስላሉ ነው።

– መሬቱን እንዴት ለዘር እንደምታዘጋጁ ማወቅ አለባችሁ።

– እንዴት አድርጋችሁ ዘር መዝራት እንዳለባችሁ ማወቅ አለባችሁ።

– እንዴት አድርጋችሁ አረም ማረም እንዳለባችሁ ማወቅ አለባችሁ።

– የደረሰውን ሰብል እንዴት እንደምትሰበስቡ ማወቅ አለባችሁ።

– የእርሻን ሥራ ለማወቅ ብዙ ቀን እንደሚያስፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለመማርም ብዙ ቀን ያስፈልጋል። 

– ለዚህም ምክንያቱ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብዙ እውነቶች ስላሉ ነው።

– የእግዚአብሔርን ቃል ለብዙ ቀናት ካደመጣችሁ ስለ እግዚአብሔር ብዙ እውነቶችን ትማራላችሁ።

– ሌላ ምሳሌ ልንገራችሁ፡

– በየቀኑ ምግብ ትበላላችሁ?

– አዎ ትበላላችሁ።

– በየዕለቱ ምግብ የምትበሉት ለምንድን ነው? 

– ምክንያቱም ሰውነታችሁ በየዕለቱ ምግብ ስለሚፈልገው ነው። 

– ሰውነታችሁ በየዕለቱ ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የእግዚአብሔርንም ቃል በየዕለቱ ማዳመጥ ያስፈልጋችኋል። 

– በየቀኑ ካልተመገባችሁ ምን ትሆናላችሁ?

– አዎ ትሞታላችሁ። 

– የእግዚአብሔርን ቃል በየዕለቱ ካላዳመጣችሁም እንዲሁ ትሞታላችሁ። 

– አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የማያውቁት ለምንድን ነው?

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለማዳመጥ ስለማይፈልጉ ነው።

– እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለማመን ስለማይፈልጉ ነው። 

– የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ የምታደምጡ ከሆነ ደስተኛ ትሆናላችሁ።

– የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ ካላዳመጣችሁ ደስተኞች አትሆኑም።

– የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ ለማዳመጥ እንደምትመጡ ተስፋ አደርጋለሁ።